Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ፓልም የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የአርማታ ብረቶች፣ የአኩሪ አተር፣ የተዳመጠ ጥጥ፣ የተለያዩ የዘሃ ክሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Feb 11, 2026)
ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆን ምርት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 005/2018
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ያወጣውን የጥራት መስፈርት ከሚያሟሉ አምራቾች እና አቅራቢዎች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ፓልም የምግብ ዘይት
- ስኳር
- የተለያየ መጠን ያላቸው የአርማታ ብረቶች
- የአኩሪ አተር
- የተዳመጠ ጥጥ
- የተለያዩ የዘሃ ክሮች
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፤
1) በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተ.ዕ.ታ ሠርቴፍኬት ያላቸው እና በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል።
2) ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ ፊት ለፊት ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00-6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00 እንዲሁም አርብ ከጠዋቱ 2፡00-5፡30 ከሰዓት በኃላ 7፡30 እስከ 11፡00 መግዛት ይችላሉ።
3) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለዛሃ ክር እና ለጥጥ፣ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እንዲሁም ለፓልም ምግብ ዘይት፣ ለስኳር፣ ለአኩሪ አተር እና ለአርማታ ብረት ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ ለብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4) የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በማሸግ እስከ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማቅረብ ይችላሉ። ከጨረታው መዝጊያ በኃላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5) ጨረታው በተመሳሳይ ቀን የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም) ከቀኑ 8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 369-2243/69-18-86