Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ስር በተለያዩ ቦታዎች ተከማችተው የሚገኙ ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Ethiopian Electric Utility
ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ግልፅ
ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር
ሰሜ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/006/2018
የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ስር በተለያዩ ቦታዎች ተከማችተው የሚገኙ ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
1 |
ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን |
የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺ ብር) |
ማሳሰቢያ፡- የእንጨት ምሶሶዎችን በተመለከተ ፈፅሞ ለማገዶነት (ለምግብ ማብሰያነት) እና ለኤሌክትሪክ መሰመር ዝርጋታ የማያገለግሉ ሲሆን ለመግዛት የሚቀርቡ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ግዥውን ፈፅመው ከወሰዱ በኃላ በሰው፣ በእንሰሳት እና በተፈጥሮ (አካባቢ) ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ በኃላፊነት መልሰው በሥራ ላይ የሚያውሉ መሆንና በዚሁ አግባብም እንደሚጠቀሙ በደብዳቤ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የትኛውም አካል እና ማንኛውም የንግድ ፍቃድ የሌለው ግለሰብ የጨረታ ሰነድ ገዝቶ የጨረታ ዋስትና በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000149984384(EEU N/A/A/R CU CON FOR EL CON) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- አድራሻ፡ ፒያሳ አቡነጴጥሮስ ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-210 በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ሰሜ አ/አ¦ሪ/ግ/ጨ/06/2018 የሚል ምልከት በማድረግ እስከ የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0941253854 መደወል ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት