በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለሥራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለሥራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 08, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቂሊንጦ ለሥራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎች አሸዋ፣ የአርማታ ጠጠር፣የግንባታ ድንጋይ፣ የሃርኮር ድንጋይ፣ የዝግባ ጣውላ የአርማታ ብረት ባለ 10፣ እስታፍ ባለ 6፣ ብሎኬት ባለ 15፣ ላሜንትድ ሚድፋ ባለ 188 ቲክነስ 2240/1220 ሚሚ፣ ቆርቆሮ ባለ 28 ጌጀ፣ አጠና ወራጅ ባለ 12 ሚሚ፣ አጠና ማገር ባለ 6 ሚሚ፣ ኮሚርስቶ ባለ (3 ሚሚ 244/1220 ሚሚ፣ ሞራሌ 50 ሚሚ /70 ሚሚ/ባለ 4 ሜትር ቁመት፣ ሞራሌ 40 ሚሚ/50 ሚሚ፣ ኤሊ ቲ ዜድ ብረት፣ የበር ሰረገላ ቁልፍ ፣ቶሪኖ ማጠፊያ መካከለኛ፣ አንተሬስት፣ የፕላስቲክ ቀለም፣ ሲሚንቶ፣ የግንብ አሸዋ፣ 02 ጠጠር፣ ገረጋንት፣ እርዳሽ፣ ተለጣፊ ማብሪያ ማጥፊያ፣ ተለጣፊ ሶኬት ሆልደር ባለ 36 ዋት ፊሎረሰንት አምፖል ባለ 18 ዋት፣ ሆለደር ባለ 18 ዋት እስታርተር ኤስ 10፣ ብሬከር ባለ 25 አምፔር፣ የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 4፣ የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 2.5፣ ኮኔክተር 150 አምፔር፣ ፓውዛ ባለ 200 ዋት፣ ሬዚስታንስ ባለ 09 እና 08፣ ናስትሮ፣ የሸክላ ባለ 58 ስፋት፣ ቦዲ ባለ 58 ስፋት፣ የተለያዩ የቧንባ እቃዎች፣ እና ብዛት ያላቸው የጥገና አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።
  2. የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
  3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
  4. የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩከ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ማዕከል የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት። ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታውላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉምየመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ማዕከል የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል።
  11. ጨረታው ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
  12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
  13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
  14. መሥሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ዝግ (የዓመት በዓል) ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴከኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- 011 471 6333 / 011 888 6089/ 011 434 8986 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቀ/ማረ/ቤትአስተዳደር / ቂሊንጦ