የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

1ኛ ዙር የ2018 ዓ.ም በጀት አመት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 001/2018

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የሎት

የአገልግሎቱ ዓይነት

የሚያስይዙት የገንዘብ መጠን

ሎት 1

የጽህፈት መሳሪያዎች

13000

ሎት 2

የኤሌክትሪክ ዕቃዎች

5000

ሎት 3

የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ በፈርኒቸር የቢሮ ማዘመን ስራ ፣መጋረጃ እና ምንጣፍ

21000

ሎት 4

የደንብ ልብስ

5000

ሎት 5

የፅዳት ዕቃዎች

6000

ሎት 6

ፎቶ ፍሬም፣ ክሪስታል ዋንጫ እና ወርቃማው ዋንጫ

3000

ሎት 7

መስተንግዶ

5000

ሎት 8

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና

4000

ሎት 9

የችግኝ ጣቢያ ግብዓት

5000

ሎት 10

የጭነት አገልግሎት /የጉልበት ስራ/

7000

ሎት 11

የተለያዩ ህትመት አገልግሎት

10000

ሎት 12

የድንኳን፣ የወንበር፣ ጠረጴዛ አገልግሎት

5000

ሎት 13

የሞንታርቦ፣ ጄኔሬተር ኪራይ እና የመድረክ ዲኮር አገልግሎት

5000

ሎት 14

የህዝብ ማመላለሻ ሀይገር ፣ የህዝብ ማመላለሻ ባስ፣ ሚኒባስና አይሱዙ የጭነት ማመላለሻ ኪራይ

5000

ሎት 15

የመኪና ጥገና፣ የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ እና የመኪና ባትሪ

10000

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን በጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  5. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎቶች ከላይ በዝርዝር በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. /CPO/ ማቅረብ የሚችሉ እና በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አምራች ካልሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መገናኛ በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 216 መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በክ/ከተማው በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስረኛው (10ኛው) የስራ ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው የስራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን።
  10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  11. ጨረታው የሚከፈተው በአስራ አንደኛው (በ11ኛው) ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መገናኛ በቦሌ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ይከፈታል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስረከቢያ በማስያዝና ከቡድን ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  13. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል።
  14. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ቦሌ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 216 ያነጋግሩን።
  • ማስታወሻ፡_ ሲፒኦ (CPO) ስታሰሩ የቦሌ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ከንስትራክሽን ጽ/ቤት/ Bole sub city CONSTRUCTION OFFIC በሚል ይዘጋጅ
  • የተሸከርካሪ መለዋወጫን በተመለከተ እንደብልሽቱ ሁኔታ የሚለወጡ ዕቃዎች ቀድሞ ለተቋሙ ለማሳወቅ ስራው ይቀጥል ተብሎ በተቋሙ ሲታመንበት የእጅ እና የዕቃ የወቅቱን ዋጋ ጨምሮ በጠቅላላ ወጪ በተጫራቹ አሸናፊ ድርጅት የሚቀርብ ሆኖ ከፍያው በተቋማችን የሚሸፈን ይሆናል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *