በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት፣ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የተሻሻሉ የወተት ላም፣ የንብ ቀፎ፣ የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣ የተመጣጠነ የእንስሳት መኖ፣ የመኪና ኪራይ፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የቤት ኪራይ አገልግሎት፣ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ የመኪና ጥገና ጋራዥ እና የመኪና ጎማ ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በዚህ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት፣ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች ፣ ፈርኒቸር ፣ የተሻሻሉ የወተት ላም፣ የንብ ቀፎ ፤ የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣ የተመጣጠነ የእንስሳት መኖ ፣ የመኪና ኪራይ ፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የቤት ኪራይአገልግሎት የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት፣የመኪና መለዋወጫ እቃ የመኪና ጥገና ጋራዥ እና የመኪና ጎማ ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1/ ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅደሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-

1.1 በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፈቃድ

1.2 የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትያለው

1.3 ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ 

1.5 ሲ.ፒ.ኦ

1.6 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና

1.7 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TI/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።

2/ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በግዥ /ፋይ /ንብ/አስ/ ደጋፊ ዳይሪክተር የስራ ሂደት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

3/ ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራችቾ ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል።

4/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና / Bank Guarantee / ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ.ፒ.ኦ (C.PO) የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናና እንዲሁም ናሙና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ ቡኃላ ወድያውኑ የውል ማስከበርያው ይመለስላቸዋል።

5/ ጨረታው ከተከፈተ ቡኃላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም።

6/ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 4፡30 ሠአት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7/ ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8/ ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 09-12-97-77-98 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ሠመራ