Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙትን የመንግስት ያገለገሉ አሮጌ የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ
ማለትም፡-
- ሎት፡- 1 ያገለገሉ አሮጌ የተለያዩ ትላልቅ ጀነሬተሮችን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 2 ያገለገሉ አሮጌ የተለያዩ ትናንሽ የውሃ ጀነሬተሮችን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 3 ያገለገሉ አሮጌ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 4 ያገለገለ አሮጌ ትልቁ ኮንቴነር ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 5 ያገለገሉ አሮጌ የተለያዩ የትራክተር ተሳቢ ጋሪዎች ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 6 ያገለገለ አሮጌ ትራክተሮችን ባለበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 7 ያገለገለ አሮጌ የእጅ ትራክተሮችን ባለበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 8 ያገለገለ አሮጌ ትልቁ የመኪና ሻንሲ ባለበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 9 ያገለገሉ አሮጌ የቦቆሎ መፈልፈያ ማሽኖችን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፡- 10 ያገለገለ አሮጌ የመመሪያ መጻሕፍቶችን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ፣
- ሎት፦11 ያገለገሉ የተለያዩ አሮጌ ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
- ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎችን ለመግዛት የሚችል ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር ብቻ /በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ህጋዊ ዕውቅና ካለው የፋይናንስ ተቋም የጨረታ ማስከበሪያ አያይዘው ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእያንዳንዱ ሰነድ 300 ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾችን የጨረታ ሰነዶቻችን ላይ የጨረታውን አይነትና ቁጥር፣ ስማቸውን ፊርማችውንና አድራሻችሁን በትክክል በመስፋር አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ዶክመንት ላይ ብቻ በፖስታ በማሸግ ሎቱን ፅፎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ 9፡00 ሰዓት በጨረታው ጥሪ በተመለከተው አድራሻ በስራ ቀን ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፣
- አሸናፊው ተጫራች መሸነፉን በደብዳቤ ካሳወቅንበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 05 የስራ ቀናት ውስጥ ፅ/ቤታችን ድረስ በመምጣት ንብረቶችን መረከብ ይኖርባችኋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 33 43 49 98 /09 26 94 49 00 /09 13 17 02 12 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Energy, cttx Generators cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Materials cttx, cttx Metal and Metal Working cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Sales, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Vehicle and Machinery Foreclosure cttx, cttx Vehicle and Machinery Sale cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Power and Electricity cttx