የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ግንባታዎች፣ ዲጅታል የልብስ ስፌት ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃዎችና ያለቀለት የጨርቅ ውጤቶች እና የቢሮ ዕቃዎችና ቁሶች መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 08, 2025)

 ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለወ/ሮ እመቤት ስዩም ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተበዳሪው /የመያዣ ሰጪው ስም

የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

 

የሐራጁ  ደረጃ

 

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ እና ቀን ሰባት

ወ/ሮ እመቤት ስዩም የወንዶች ልብስ ስፌት

በኦሮሚያ ብ/ክ/ መንግስት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ በ876 ካሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ ዲጅታል የልብስ ስፌት ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃዎችና ያለቀለት የጨርቅ ውጤቶች እና የቢሮ ዕቃዎችና ቁሶች

61,041,737.69 2018 ዓ.ም

1ኛ

በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የውስጥ ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም.  ከ 4፡30-6፡30 ሰዓት

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ ¼ ኛ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ ለባንኩ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪ ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
  3. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
  4. የጉምሩክ ቀረጥና ታከስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
  5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  6. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
  7.  በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።
  8. ከፕሮጀክቱ ጠቅላላ ይዞታ 1.8 ሜትር ለኮሪደር ልማት በአሰላ ከተማ መስተዳደር የሚቀነስ መሆኑ እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት የሚችል ሲሆን ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት ናፍራን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-212 0417 ላይ መደወል ይችላሉ።
  9.  ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሐራጁ አይገደድም።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት