Your cart is currently empty!
ብርሃን ለሕፃናት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ፣ የሞተር ብስክሌት፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ተሽከርካሪ የቢሮ ወንበሮች፣ ፕሪንተር፣ የወረቀት መብሻ እና ድርጅቱ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ያሉ የሒሳብ ሰነዶች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃን ለሕፃናት የማህበረሰብ ተሃድሶን መሰረት በማድረግ ሕፃናት ተኮርና የአካል ጉዳትን ያማካለ ሁለገብ አገልግሎት ለመስጠት እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 1997 የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡
በመሆኑም ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 22 በጥቂት ቀበሌዎች የተጀመረው ሥራ ዛሬ ላይ በአምስት ክልሎች ማለትም በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ፣ በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማና ኃይቅ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቢሾፍቱ ከተማና በአድአ ወረዳ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሃዲያ ዞን፣ በአፋር ክልላዊ መንግስት፣ በሲዳማ ክልል በሃዋሳ ከተማ እና በመልጋ ወረዳ ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ ለአካል ጉዳተኛና በተለያዩ ምክንያቶች ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሕፃናትን ለማብቃት የድርሻውን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ድርጅታችን ብርሃን ለሕፃናት
- 1 አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ረጅም ዓመት ያገለገለ (እ.ኤ.አ. የ1989 ሞዴል ስሪት)፣
- 6 (ስድስት) የሞተር ብስክሌት፣
- 9 ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣
- 2 ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣
- 2 ተሽከርካሪ የቢሮ ወንበሮች፣
- 1 ፕሪንተር፣
- 1 የወረቀት መብሻ፣
- ድርጅቱ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ያሉ የሒሳብ ሰነዶች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉና በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ፡–
1. በዘርፉ የታደሰ የሥራ (የንግድ ፈቃድ) ያላቸው፤
2. ከዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ አንድ ፐርሰንት (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፤
አድራሻ፡– ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከታች ከተገለፀው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመውሰድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 ተከታታይ ከቀናት ማለትም (ከሰኞ 03/02/2018 ዓ.ም እስከ እሁድ 07/02/2018 ዓ.ም) ውስጥ ሞልተው ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡ ሜክሲኮ አደባባይ ከፖሊስ ሆስፒታል ጀርባ አልሳም የመኖሪያ መንደር ፊት ለፊት ከብስራት ሆቴል አጠገብ ብርሃን ለሕፃናት ህንፃ፣ ስልክ ቁጥር፡– 011-554-4814/ 45/ 09-22-72-09-20 ያሳውቁን፡፡
ብርሃን ለሕፃናት