Your cart is currently empty!
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በድርጅቱ በ2018 ዓ.ም የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት፣ የደረቅ ትራንስፖርት ማጓጓዣ አገልግሎት፣ ያገለገሉ መኪናና የእርሻ ትራክተር ከነማረሻው የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ፣ የምርጥ ዘር መቋጠርያ ፖሊ-ባጎችን ለማሠራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/18 ዓ.ም/ ገዥ፣ የአገልግሎት እና ሽያጭ/፡–
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በድርጅቱ በ2018 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሸጥ ይፈልጋል።
- የ2017/2018 ዓ.ም የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ፦
- የደረቅ ትራንስፖርት ማጓጓዣ አገልግሎት ጨረታ፡– ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ/፡
- ያገለገሉ መኪናና የእርሻ ትራክተር ከነማረሻው የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ፡–
- የምርጥ ዘር መቋጠርያ ፖሊ–ባጎችን ለማሠራት/ ለመጀመሪያ ጊዜ
በዚሁም መሠረት
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የመንግሥት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ማስያዝ ያለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ገንዘብ መጠን በጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶች ላይ የሚገለፅ በመሆኑ (በደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ስም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ድረስ ለደረቅ ትራንስፖርት ማጓጓዣ አገልግሎት ብቻ እና ለተቀሩት ጨረታዎች 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ሀዋሣ ከተማ በሚገኘው በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ በተገለፁት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማንኛውም ማሸጊያ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው እና በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 10ኛው እና 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል።
- ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቹ ጨረታዉን ከመሳተፍ ይታገዳል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፈርማቸውን እና የድርጅታቸዉን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046 220 5992
ሀዋሳ
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
Accounting System Design cttx, cttx Accounting and Auditing, cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Freight Transport cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Others cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Plastic Raw Materials cttx, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Rent cttx, cttx Sales, cttx Transportation Service cttx, cttx Vehicle and Machinery Foreclosure cttx, cttx Vehicle and Machinery Sale cttx, cttx Vehicle cttx, cttx Warehousing, Disposals and Foreclosure cttx, Transit and Transport Service cttx