Your cart is currently empty!
በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት የተሸከርካሪዎች የመኪና እቃ መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማ ለመግዛት እና አሮጌ ብረታ ብረቶችን በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግንብ/አስ/ ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ
- የተሽከርካሪ ሞዴል LAN-25፤1Hz-78 1Hz-79 ተሸከርካሪዎች የመኪና እቃ መለዋወጫ የመኪና ጎማ በመደበኛ በጀት በበጀት ዓመቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ፣
- አሮጌ ብረታ ብረቶችን በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
ስለሆነም፡-
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ያላትና ግብር የከፈለች
- የሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል
- በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው /ያላት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያለው/ያላት
- ውድድሩ በድምር ውጤት ሎት ሲሆን የውለታው ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ በበጀት ዓመቱ ሊሆን ይችላል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ለአሮጌ ብረታ ብረት ሽያጭ የንግድ ፈቃድ የቫት ተመዝጋቢ ወዘተ ሳያስፈልግ ማንኛውንም ሰው ድርጅት መጫረት የሚችል መሆኑን ይገንዘቡ የብረታ ብረት ሽያጭን በተመለከተ ሽያጭ በኪሎ ሲሆን የአንድ ኪሎ መነሻ ዋጋ የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ መሆኑን እንገልፃለን። የተወዳደሩበትን አርጌ ብረታ ብረት አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ገቢ ሲያደርጉ ንብረትዎን ይረከባሉ በተባሉ ጊዜ ቀርበው ገንዘቡን ገቢ ባያደርጉ ለጨረታ ማስረከቢያ ያስያዙት ሲፒኦ ተወርሶ ወደ መንግስት ካዝና የሚገባ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ከጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2% በጥሬ ገንዘብ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱን አልብኮ ወረዳ ዝጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ በመገኘት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህንን ማስታወቂያ የያዘው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ በመቆየት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ተከታታይ ቀናቶች ይሆናል።
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
- በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ፣ ማብራሪያ ወይም ቅሬታ ካለዎት በጉና በአዋጁ መሰረት በአልብኮ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 /11/ በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 033215003209
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Disposal Sale cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Sales, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Metals and Aluminium cttx