በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት የፕላንና ልማት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ (Electronics items/ ኤሲ) እና ፋይል ካቢኔት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2015

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት የፕላንና ልማት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ

  1. ሎት፡- 001 ኤሌክትሮኒክስ (Electronics items/ ኤሲ
  2. ሎት፡- 002 ፋይል ካቢኔት በግልጽ ጨረታው አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መስረት ከላይ የተጠቀሱት ቋሚ ዕቃዎች ለማቅረብ መወዳደር የምትፈልጉ

 ተጫራቾች፦

  1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውና የዘመኑን እንቅስቃሴ የሚያመለክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 71 መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎች ዝርዘር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለጨረታ ዋጋ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ኦርጅናልና ኮፒ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባትይጠበቅባቸዋል።
  8. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞከር ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከመወረሰም በላይ በሌሎች ጨረታዎች እንዳይሳተፍ ዕገዳ የሚጣልበት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ሠነድ ማስገቢያ ሣጥን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ ንብ/አስ/ ቡድን መሪ ቢሮው ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡-09 12 46 67 04 / 09 17 16 51 45 ይጠቀሙ።

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መን⁄ የፕላንና ልማት ቢሮ