Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተለያዩ ማሽነሪዎችንና ሌሎች መሳሪያዎችን ባሉበት ጨረታ መሸጥ/ማከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ደንበኛ የነበሩ ምንተስኖት ወ/አማኑኤል በሊዝ ፋይናንሲንግ ሥርዓት በዱቤ ግዢ እና ኪራይ ውል ከባንኩ የተከራዩትን የካፒታል ዕቃ ማሽነሪዎች ላይ የውል ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተገለጹ የተለያዩ ማሽነሪዎችንና ሌሎች መሳሪያዎችን ባሉበት ጨረታ መሸጥ/ማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተከራይ ስም |
በሐራጅ የሚሸጠው/የሚከራየው ንብረት የሚገኝበት ቦታ
|
የንብረቱ ዝርዝርና አይነት
|
የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)
|
የሐራጁ/የጨረታው ደረጃ
|
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ም ን ተ ስ ኖ ት ወ/አማኑኤል
|
ኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ፉሪ ክ/ከተማ፣ ጨፌ ክራቡ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ሶዶ ጅዳ ህንፃ
|
1. Aksa Diesel Generator (150KVA, MFY 2023) (Quantity -1) 2. Bread slicer (Quantity –1) 3. Mixer (Quantity -1) 4. Volumetric Dough Divider (Quantity –1) 5. Dough Moulder Machine (Quantity -1) 6, Rotary Oven Doiner Firin Tray (Quantity –1) 7, Proofer for rotaty oven with steam generator (Quantity –1) 8. French Bread Tray & Trolley /With 16 French bread treys/ (Quantity -2) 9. Flat Trey with Trolley With 16 flat treys/ (Quantity -2)
|
7,448,457.00
|
2ኛ ዙር ሐራጅ
|
ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ሰዓት
|
የሐራጁ መመሪያ፤
1. የተመለከተውን ንብረቶች ለመግዛት ወይም ለመከራየት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህብራት/ኢንተርፕራይዝ) የጨረታውን የመነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25 በመቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በተዘጋጀና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በማቅረብ ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይካሄዳል።
3. ጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
4. የጨረታ አሸናፊ የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተ.እ.ታ (VAT) ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት።
5. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ቀሪውን ገንዘብ ተ.እ.ታን ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ንብረቱ አሸናፊው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
6. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት በወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈለገውን የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ መክፈል ግዴታ አለበት።
7. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል የጨረታውን አሸናፊ ከሆነና ንብረቱን በባንኩ ማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ መሰረት የመከራየት ዕቅድ ካለው የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት ማሟላት ይጠበቅበታል።
8. አሽናፊው ተጫራች ንብረቱን በማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ ውል ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ በባንኩ አሰራር መሰረት ቅድሚያ ክፍያን በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመክፈል የባንኩን የማሽነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ መስፈርት በማሟላት ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
9. ስለ እያንዳንዱ ንብረት ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ተኛ ወለል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪከት ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር +251-11-558-6175 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
10. ንብረቶቹን ለመጎብኘት ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይቻላል።
11. ባንኩ ተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ