Your cart is currently empty!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 01 የጽ/መሣሪያ፣
- ሎት 02 የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 03 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 04 የቧንቧ እቃዎች፣
- ሎት 05 የፕላስቲክ /HDP/ ቧንቧ እቃዎች፣
- ሎት 06 ጣውላ፣
- ሎት 07 ሲሚንቶ፣
- ሎት 08 ቆርቆሮና ሚስማር እና የተፈበረኩ ብረታ ብረቶች፣
- ሎት 09 ፈርኒቸር፣
- ሎት 10 የመኪና እቃ መለዋወጫ፣
- ሎት 11 የመኪና ጎማ፣
- ሎት 12 የማሽን ኪራይ፣
- ሎት 13 አስተዳደር የቢሮ ግንባታ፣
- ሎት 14 የሻይ ክበብ/ መናፈሻ ግንባታ፣
- ሎት 15 ም/ቤት የቢሮ ግንባታ፣
- ሎት 16 የአጥር ግንባታ በመደበኛ እና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት በእያንዳንዱ ሎት በተናጠል በዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች ከሎት 01 እስከ ሎት 11 ላሉት እቃዎች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / ከሎት 12 የማሽን ኪራይ እና ለሁሉም ግንባታዎች የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፍል ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ 1.5% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ሎት 01 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 02 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 03 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጠዋት 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በዚሁ ቀን ከሰዓት ሎት 04 የቧንቧ እቃዎች፣ ሎት 05 የፕላስቲክ /HDP/ ቧንቧ እቃዎች፣ ሎት 06 ጣውላ፣ ሎት 07 ሲሚንቶ፣ ሎት 08 ቆርቆሮና ሚስማር እና የተፈበረኩ ብረታ ብረቶች እና ሎት 09 ፈርኒቸር 8:00 ታሽጎ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እንዲሁም በ17ኛው ቀን ሎት 10 የመኪና እቃ መለዋወጫ፣ ሎት 11 የመኪና ጎማ፣ ሎት 12 የማሽን ኪራይ ጠዋት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሎት 13 አስተዳደር የቢሮ ግንባታ ሎት 14 የሻይ ክበብ/ መናፈሻ ግንባታ፣ ሎት 15 ም/ቤት የቢሮ ግንባታ፣ ሎት 16 የአጥር ግንባታ ጨረታውን በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ22ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
6 ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
7. አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች መጋዝን ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይችሉም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለባቸው፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ሙሉ የመስረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የተሞላው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር ዝቅትኛ ቀን 40 ቅናት ላይ ጸንቶ ይቆያል።
12. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 033 336-1249 ወይም 09-13-66-97-14/09-12- 37-09 84 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት