Your cart is currently empty!
የጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአዳራሽ ግንባታ በርና መስኮት፣ የውሃ እቃዎች እና ሲሚንቶ እና የመኪና ጎማ መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለጉና በጌምድር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት እና በሰቆጣ በጀት
- ሎት 1 ለአዳራሽ ግንባታ በርና መስኮት፣
- ሎት 2. የውሃ እቃዎች እና ሲሚንቶ እና
- ሎት 3 የመኪና ጎማ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1.ብር 8,000፣ 2ኛ. ለሎት 2. ብር 10,000 ፤ ለሎት3 ብር 10,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በማስቆረጥ በማስያዝ መረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ከጥር 25/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- የዋጋ ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚሞሉበት ሰዓት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ መነካካት እና ሁለት አይነት ዋጋ ማስቀመጥ የለባቸውም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በዋጋ መሙያ መሰረት በሎት በጠቅላላ ድምር ብቻ ነው ከዚህም በተጨማሪ አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀን ውስጥ ያሸነፉበት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በማስቆረጥ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርበው ውል መውሰድ ካልቻሉ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሰረት
አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ - መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠመረጃ በስልክ ቁጥር 058 251 02 26 ደውለው አስፈላጊውን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx Metal and Metal Working cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Plastic Raw Materials cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Metals and Aluminium cttx