የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና ቋሚ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ የተሽከርካሪዎች

መለዋወጫዎች እና ቋሚ ዕቃዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር OACE, AMF/MS/02/2018

የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ

  • የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤
  • የተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና
  • ቋሚ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት እለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ 1000043405229 ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስክ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡00- 6:00 ሰዓት ድረስ አሰላ ቁሉምሳ በሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 05) ወይንም አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረላት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በአየር ላይ ከፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  5. ተጫራቾች በኢንቨሎፕ የታሸገ የጨረታ ሰነዳቸውን በአሰላ ብቅል ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 051 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  6. ጨረታው በዕለቱ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሰላ ቀለምላ በሚገኘው የፋብሪካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ዕቃዎቹን ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተለገጹት የሥራ ቀናት አሰላ ቁሎምሳ በሚገኘው የፋብሪካው ቅጥር ግቢ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ጨረታ ሰነዳቸውን የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ፣

ስልከ ቁጥር፤ 022 331 52 66 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

የኦሮሚያ ገብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት

ፌዴሬሽን ኃ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ