Your cart is currently empty!
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ንብረቶች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-26/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፤ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች : የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይከሎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2 ማንኛዉም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡ ዐዐ ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100( አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
3. ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች እና ያገለገሉ ሞተርሳይክሎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛዉም እድሜዉ ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጲያዊ መወዳደር ይችላል።
4. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5%(አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች ለመገናኛ ዕቃዎች ለመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ እና ለሞተር ሳይክል ለእያንዳንዱ ኮድ ብር 50,000(ሀምሳ ሺህ)፤ ለተሸከርካሪዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 1,000,000(አንድ ሚልዮን ብር) የጨረታ ዋስትና ( C.P.O) ለእያንዳንዱ የጨረታ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5.ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛዉ) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛዉ) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልፅ ጨረታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሀራጅ ጨረታው ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል እና እሑድ ቀን የሚውል ክሆነ የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ ይሆናል።
6 ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበዉ ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያተረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ክነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
7- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃ አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ። በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠዉን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
8 ማንኛዉም ተጫራች የሰጠዉ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ዉጤት እስከሚያሳዉቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
9 ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈት በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ክሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
10.ተጫራቾች የዕቃዉን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
11.ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ይህንን ባያደርጉ ጨረታዉ ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ፅቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/ 046-212-65-95
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት