Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ብረታ ብረቶችን፣ ጎማዎች እና ፕላስቲኮች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ብረታ ብረቶችን፣ ጎማዎች እና ፕላስቲኮች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ፡–
- የጨረታ ማስከበሪያ 7,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ካሽ ማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አስር / ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡–
- ንብረቱን ማየት የሚፈልግ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 7ኛው ቀን ውስጥ ድረስ በአካል ማየት ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 771 0211 ይደውሉ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
cttx Disposal Sale cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Sales, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Metals and Aluminium cttx