በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ መገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10-2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ /ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ

  • የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣
  • የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
  • መገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣
  • የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
  • የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣
  • ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ እድሜው 18 በላይ የሆነ ከተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተ/ቁጥር 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  3. ከላይ በተ/ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም አያስፈልግም።
  4. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2018 . ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ 2፡00 እስከ 600 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤
  5. ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 10/2018 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ 200 እስከ 600 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ /ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ፣
  6. የግልፅ ጨረታው የካቲት 10/2018 . ከጠዋቱ 345 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ /ቤቱ ቢሮ ቁጥር 501 ይከፈታል፣
  7. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ /ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረገበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ የካቲት 10/2018 . ከጠዋቱ 345 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
  8. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል
  9. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
  10. ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (5%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5/በአምስት ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፤
  12. ከላይ በተ/ 11 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻለ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
  13. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም፣
  14. ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣
  15. በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስመ ንበረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ /ቤቱ አይሸፍንም፤
  16. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
  17. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ//ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058-320-74-18/058-320–75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻበአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ /ቤት