የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያላገለገሉ እና ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች ከሎት አንድ እስከ ሎት አስራ አራት በመከፋፈል ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 11, 2026)

የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታሠቂያ

የጨረታ ቁጥር DIS 01/2018

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ

  • ያላገለገሉ እና ያገለገሉ የተለያዩ አይነት የከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የመካከለኛ እና
  • የቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች ያገለገሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች 
  • ያገለገሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮች
  • የተለያዩ ስቴሽነሪዎች፣
  • የተለያዩ አልባሳቶች እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ከሎት አንድ እስከ ሎት አስራ አራት በመከፋፈል ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የጨረታ ሰነድ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም በዚህ የግልፅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከገቢዎችና ጉምሩክ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ ማቅረብ የቻለ እና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የተመላከቱትን አስገዳጅ ዝርዝር መመዘኛዎች ማሟላት የቻለ በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይችላል።

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሐሙስ የካቲት 19 ቀን 2018ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመክፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል።

ከሎት አንድ እስከ ሎት አስራ አራት የቀረቡ የተለያዩ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት በቃሊቲ ትራኪንግ እና በቃሊቲ ጋራዥ መጋዘን በአካል በመሄድ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ።

ጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት የካቲት 19 ቀን 2018ዓ.ም ከ8፡00 ሰዓት በፊት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ወይም በኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሠዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋመ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549304/0906329086 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና

ሎጅስቲክስ