የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 14, 2026)

 የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደሩትን የብድር ገንዘብ በውላቸው መሠረት መክፈል ስላልቻሉ ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመያዣ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም

 ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

 የሚሸጠው ንብረት አይነት

የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ

ቀሪ የመሬት ሊዝ ውል ()

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)

የሐራጅ ደረጃ

 

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት

1

ድላ አብርሃ እርሻ ልማት

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ኢታንግ ልዩ ወረዳ ዋንኬ ቀበሌ

የእርሻ መሬት

500 ሄክታር መሬት ላይ የተቋቋመና 474.60 ሄክታር የለማ የእርሻ መሬት ያለው

35

22,139,653.67

 

2

ምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሕንፃ ግንባታዎች

ሁለት የሠራተኞች መኖሪያ ቢሮ፣ ሁለት መጋዘን፣ ጋራጅ እና የጥበቃ ቤት ያለው

የእርሻ መገልገያ መሳሪያዎች

1, አንድ DEUTZ- FAHR ትራከተር 70HP 2011 ስሪት

2 ሁለት ባለ 24 አንድ ዲስክ መከስከሻ

3 አንድ ባለ 4 ዲስከ ማረሻ

4. ሁለት መዝሪያ (Planter)

5 አንድ ኬሚካል መርጫ

 

ተሸከርካሪዎች

1 ባለ ሁለት ጋቢና ቶዮታ ፒካፕ ተሽከርካሪ 2014 ስሪት

2, አንድ የደረቅ ጭነት አይሱዙ/SUZU FSR ተሽከርካሪ

 

 

 

 

2

ደሳለኝ መብራቱ እርሻ ልማት

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ኢታንግ ልዩ ወረዳ እኛሌ ቀበሌ

የእርሻ መሬት

402 ሄክታር መሬት ላይ የተቋቋመና 207. 40 ሄክታር የሰማ የእርሻ መሬት ያለው

34

9,903,189.28

በመጀመሪያ ደረጃ

 

ጋምቤላ ዲስትሪከት ግንቦት 06 ቀን 2018 .ከቀኑ 800 እስከ 1000 ሠዓት

 

ለልዩ ልዩ አገልግሎት የተገነባ የሕንፃ ግንባታዎች

የሠራተኛ የመኖሪያ ቢሮዎች፣ መጋዘን እና የመጸዳጃ ቤት ግንባታዎች ያሉት

 

የእርሻ ትራክተር

አይነቱ ፈርጉሰን ሞዴሉ MF460 የምርት ዘመን 2014, የብራዚል ምርት የሆነ

 

 

  1. የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% ሃያ አምስት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
  2. በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች ከድርጅቱ የተሰጠውን ውክልና እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።
  3. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል
  4. በሐራጅ ሽያጭ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።
  5. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15 /በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል።
  6. በሐራጁ ለተሸናፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  7. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የባለቤትነት ስም ማዛወሪያ ጨምሮ ይከፍላል። ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ
  8. ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በስልክ ቁጥር፡ +251475512588 ወይም +251471518284 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
  9. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም የሐራጁ ተሳታፊዎች ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር የጉብኝት ፕሮግራም ቀጠሮ በማስያዝ ፕሮጀክቱን መጎብኘት ይችላል።
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *