የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ እስካቫተር (EXCAVATOR) ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ እስካቫተር (EXCAVATOR) ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Apr 15, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ እስካቫተር (EXCAVATOR) ተሸከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ጨረታ የቀረበውን ተሽከርካሪ ከቀን 09/08/2018 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ሳይ መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች

1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤

2. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተሽከርካሪ ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል

3. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤

5. ተሽከርካሪ አሽንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፤

6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤

9. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤

10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 09/08/2018 ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 13/08/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

N.B:-

  • አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
  • የቻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያመጠ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃልን።

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *