Addis Zemen (Apr 30, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር የተለያዩ የስልጠና ዕቃዎችን ማለትም፡
- አግሮ ፕሮሰሲንግ ዕቃ
- አውቶሞቲቪ ዕቃ
- ብረታ ብረት
- የቤትና ቢሮ/ፈርኒቸር ዕቃዎች
- የጽህፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን
- የኮንስትራክሽን ዕቃዎች
- የጋርመንትና የደንብ ልብስ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች።
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ VAT ሰርተፍኬት ያለው
- በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ/የድረ– ገጽ ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን የግብር ግዴታዎችን ስለመወጣታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ማለትም፡–
- የእያንዳንዱን ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 104 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና ኮሌጁ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ሞልተው በማስገባት መወዳደር ይቻላል።
- የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፐ ኦርጅናልና በ1 ኮፒ በጨረታ ሳጥኑ መጨመር ያለበት ሲሆን ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ ድርጅቶች ሲፒኦን በጥቅል ማድረግ ሲችሉ ሌሎች ሰነዶችን በእያንዳንዱ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ካለሸጉ ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በማስላት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ጋራንት እና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጠቅላላ ዋጋ ከ1% በታች የሚያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ። አሸናፊዎች በቅድሚያ 10% ውል በመግባት የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ጋራንትና ሲፒኦ በማስያዝ ውልይገባሉ። አሸናፊ ድርጅቶች ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆኑ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይደረጋል።
- ኮሌጁ ከአሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃ የሚረከበው ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ ግቢ ብቻ ስለሆነ ጨረታውን የሚያሸንፉ ድርጅቶች ያሸነፉትን ሙሉ ዕቃ እስከ ኮሌጅ ግቢ በማምጣት የሚያስረክቡ ይሆናሉ። የዕቃዎቹም ጥራትና ዓይነት በኮሌጁ ባለሙያዎች ተረጋግጦ ተቀባይነት ካላገኘ ኮሌጁ ለመረከብ አይገደድም።
- ጨረታው የሚታሸግበት ቀንና ቦታ፡– ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ሲሆን 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- የሚከፈትበት ቀንና ቦታ ወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ የጨረታ ሰነዱ ተሽጦ በተጠናቀቀበት በ2ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ቼክና ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸውን ስፔስፊኬሽን መቀየርና መደለዝ እንዲሁም የተደለዘ የተጫራች ሰነድ ተጫራቾችን ከጨረታው ውጪ ያደርጋቸዋል።
- ድርጅቶች ተገቢውን አድራሻ ማህተም ስልክ እና የፋክስ ቁጥርን ጨምሮ በሰነዱ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር | 09 12 11 13 40 / 09 13 30 24 99/ 09 16 71 51 14 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ