የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በጎፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ለሣዉላ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ360 ተማሪዎች መቀመጫ ወንበር በቀረበዉ 3 ገጽ የወንበር ዲዛይን ስፔሲፊኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ወይም ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በጎፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ለሣዉላ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ360 ተማሪዎች መቀመጫ ወንበር በቀረበዉ 3 ገጽ የወንበር ዲዛይን ስፔሲፊኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ወይም ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በጎፋ ዞን አስተዳደር / ቤት ለሣዉላ 2ተኛ ደረጃ /ቤት 360 ተማሪዎች መቀመጫ ወንበር በቀረበዉ 3 ገጽ የወንበር ዲዛይን ስፔሲፊኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ወይም ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ NATተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው፣
  5. የዘመኑን ግብር የከፈለበት ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፣
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ/CPO/ 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ /ብር ማቅረብ የሚችል፤
  7. ባለፉት ሁለት አመታት በተመሣሣይ ሥራ የሰራበት የመልካም አፈፃፀም ማስረጃ ከመንግሥት /ቤቶች የተሰጠውን ማቅረብ የሚችል።
  8. ተጫራቾች ከላይ ከ1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፣
  9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ከጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ያገኛሉ።
  10. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈዉን የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር በራሱ ወጪ አስከ ሳዉላ ከተማ ጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ንብረት ክፍል አምጥቶ ማስረከብ አለበት።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ 16ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4:30 ጨረታው ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፦

  • ጨረታዉን ያሸነፈው ተጫራች ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ማስረከብ የሚችል።
  • ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ሥራውን በዲዛይኑና በተዘጋጀው ስፔሲፊኬሽን
  • መሠረት መስራቱን በባለሞያ ሲረጋገጥ ብቻ የምንረከብ መሆኑን ጭምር እናስታውቃለን
  • /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለተጨማሪ ማብራሪያ፡የስቁ 09-13-32 97-28 ይደውሉ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት

የጎፋ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *