የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 01, 2026)

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር PPS/VP-18FBI/10/08/2018

የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የቤተመንግሥት አስተዳደር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ደን ልማት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲአትር፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ ፍትሕ ሚኒስቴር፣ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን፣ የኢንተርፕራይዝ ልማት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።

1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል።

2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት /ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4.ተጫራቾች ለሚገዙት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ነገር ግን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ያልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ነገር ግን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

6. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ ዕዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የጉምሩክ ቀረጥ ግብር እዳ፣ የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው የሚሸፈን ይሆናል።

7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 415 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።

8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 (ሰባት) የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

10. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።

11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ፡ የተቋማችንን ድህረገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ

የፌዴራል መንግሥት ግዥ አገልግሎት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *