Reporter (May 24, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ
Ethio Life and General Insurance S.C
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሸከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን ለመግዛት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ክራውን ሆቴል ጀርባ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት መኪና ማቆያ ወረድ ብሎ ኩባንያው አዲስ ባስገነባው ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery Site) ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት የሥራ ቀናት በመምጣት ማየት ይቻላል።
2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላትን ቅሪቶችን የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቶሊፕ ሆቴል ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይቻላል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ማዘዣ ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታው አሸናፊዎች የተሽከርካሪውን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የጨረታ ውጤት በተገለፀ በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው በአሥር ቀናት ውስጥ ንብረቱን ከግቢው ማንሳት ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት አይቻልም:: የጨረታ ዋጋ አባዝቶ ማቅረብ አይቻልም።
6. ተሽከርካሪው በጨረታ እስከ ተሸጠበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙ አይጠየቁበትም። ተሽከርካሪው ከተሸጠ በኋላ የሚፈለግ ግብር ታክስና እንዲሁም ተሸከርካሪው ላይ የሚፈለግ የቦሎ ክፍያና ተያያዥ ቢኖር የገዥው ኃላፊነት ይሆናል።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልፅ ሁኔታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ነገር ግን ባላቀረቡት ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ።
9. ተጫራቾች ስለተሽከርካሪዎቹ መንገድ ትራንስፖርት በሰጠው ውሳኔና በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549650/0911157195/0911153169 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።