Reporter (Jun 10, 2026)
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶች
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AFDAO-37/2026
አክሽን ፎር ዴቬሎፕመንት /ACTION FOR DEVELOPMENT/ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች፣ እንዲሁም የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የቢሮ ዕቃ፣ የቢሮ የሥራ መሣሪያዎችንና “Tyres & Batteries” ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም፡–
ሀ. ሞተርሳይክሎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስትመቶ ብር) በመክፈል፣
ለ. የቢሮ ዕቃዎች፣ የቢሮ የሥራ መሣሪያዎችንና Tyres & Bateries” መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል፣
ሐ. በፊደል ተ/ቁ “ሀ” እና “ለ” የተጠቀሱትን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች ደግሞ፣ ለሁለቱም የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል፣
ለእያንዳንዳቸው የተዘጋጀውን የጨረታ ስነድ (የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ) 22 ማዞሪያ ከጎላጎል ህንፃ ወደ ቦሌ መድሃኒ ዓለም በሚወስደው መንገድ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል 100 ሜትር ወረድ ብሎ ወደ ቀኝ በሚታጠፈው መንገድ በመጓዝ ከቅዱስ ማርቆስ ት/ቤት ፊትለፊት ሲደርሱ ወደ ግራ 50 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው የድርጅቱ ግዢ ክፍል በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ፡–
1. ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ያገለገሉ የቢሮ ዕቃ፣ የቢሮ የሥራ መሣሪያዎችንና Tyres & Batteries” ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝቶ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት/ማየት ይችላል::
2. ለሞተር ሳይክሎች ግዢ ተጫራቹ የሚያቀርበውን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ቁጥር “AFDAO 37/A” “የሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ያገለገሉ የቢሮ ዕቃ፣ የቢሮ የሥራ መሣሪያዎችንና Tyres & Batteries” የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመመላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ አስገብቶ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል::
3. ለቢሮ ዕቃ፣ ለቢሮ የሥራ መሣሪያዎችና “Tyres & Batteries” ግዢ ተጫራቹ የሚያቀርበውን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ቁጥር “AFDAO-37/B” “የቢሮዕቃዎች፣ የቢሮ የሥራ መሣሪያዎችና “Tyres & Batteres” የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ” ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ አስገብቶ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል::
4. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚጫረትበት ሞተር ሳይክል እንዲሁም “የቢሮዕቃዎች፣ የቢሮ የሥራ መሣሪያዎችና “Tyres & Batteries” የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምታቸውን 10% የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአክሽን ፎር ዴቬሎፕመንት /ACTION FOR DEVELOPMENT/ ድርጅት ስም አሠርቶ ከጨረታው ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ አለበት:: በሚያስገቡት ፖስታ ላይም የተጫራቹ ሙሉ ስምና አድራሻ መገለፅ ይኖርበታል::
5. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ወይም በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው::
6. ጨረታው ለሞተር ሳይክሎች ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሁም ለቢሮ ዕቃ፣ ለቢሮ የሥራ መሣሪያዎችና “Tyres & Batteries” ደግሞ፣ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል::
7. ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ፣ የሚቀርቡ ማናቸውም የመወዳደሪያ/ መጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::
8. ያለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
9. በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የጨረታው የግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ፣ የሚመለስላቸው ሲሆን፣ የጨረታው አሸናፊዎች ደግሞ፣ ያስያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ንብረት ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል::
10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠናቅቆ በመክፈል ሞተር ሳይክሎቹንም ሆነ ሌሎች በጨረታ ያሸነፈባቸውን ንብረቶች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሳ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በቅጣት መልክ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::
11. አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ሞተር ሳይክልም ሆነ ዕቃ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ::
12. አሸናፊ ተጫራቾች ከስም ዝውውር ጋር በተያያዙ የሚደረጉ ክፍያዎችን፣ የመንግስት ቀረጥና ታክስ እንዲሁም ማንኛውንም ተዛማጅ ወጪዎችን ይሸፍናሉ::
13. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-662-59-76 / 0939 655 371 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል::
አክሽን ፎር ዴቬሎፕመንት /ACTION FOR DEVELOPMENT/