አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለቴሌቪዥን መገጣጠሚያ ሲገለገልበት የነበረውን ማሽን እንዲሁም የተለያዩ ያገለገሉ የፋብሪካ ማምረቻ መስመር መገጣጠሚያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ መፈተኛ ማሽኖችን፣ ኮምፒውተሮችን እና የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለቴሌቪዥን መገጣጠሚያ ሲገለገልበት የነበረውን ማሽን እንዲሁም የተለያዩ ያገለገሉ የፋብሪካ ማምረቻ መስመር መገጣጠሚያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ መፈተኛ ማሽኖችን፣ ኮምፒውተሮችን እና የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jun 17, 2026)

የጨረታ ቁጥር ጨ001/18

አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለቴሌቪዥን መገጣጠሚያ ሲገለገልበት የነበረውን ማሽን እንዲሁም  የተለያዩ ያገለገሉ የፋብሪካ ማምረቻ መስመር መገጣጠሚያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ መፈተኛ ማሽኖችን፣ ኮምፒውተሮችን እና የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የዕቃዎቹን ዓይነትና ሁኔታ ማየትና በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ምዝገባ ቁጥር ሰነድ ያላቸው፣ በሙሉ ከዚህ በታች ያሉትን መመሪያዎች በመከተል መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. የዕቃዎቹን ዓይነትና ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል አራት ኪሎ በሚገኘው የድርጀቱ ዋና መ/ቤት የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመውሰድ ዕቃዎቹ ባሉበት ሄደው ማየት ይችላሉ።

2. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰበታ አልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ በሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል።

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ይዞታ በማየት የሚሰጡትን ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም በፊደልና በቁጥር የተጻፈው ዋጋ ልዩነት የሚኖረው ከሆነ መ/ቤቱ ትልቁን ዋጋ በመያዝ ጨረታውን ያወዳድራል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሞልተው የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (20%) ጨምሮ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ላይ አራት ኪሎ ዋናው መ/ቤት ይከፈታል።

6. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።

7. የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ከከፈለ በኋላ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረታቸውን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባያንው ገቢ ይደረጋል።

8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።