2merkato.com (Jul 11, 2026)
ዘመን ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ ማስታወቂያ
ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 10 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ደንቦች፣
1. ሞተር ሳይክሎቱን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾት ከሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሞተር ሳይክሎቹን ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ ወይም በስልክ ቁጥር 0115 57 58 25/ 011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አስተዳደርና ሎጂስቲክስ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የመረጡትን ሞተር ሳይክል/ሎች ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በባንኩ ህንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
6. አሽናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት። ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
7.ባንኩ ንብረቱን በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
8. ከስም ዝውውር ፣ እንዲሁም ሞተሮቹን ከማስተካከል ከመጫንና ከማጋዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል።
9. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል።
10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘመን ባንክ አ.ማ.