Addis Zemen (Aug 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች እያንዳንዱ ተጫራች እንዲያከብር ይጠይቃል።
1. ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ ወ/7 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ሎት1/ ደንብ ልብሶች ሎት/2 የጽዳት እቃዎች ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 4 ልዩ ልዩ እቃዎች ሎት/5 የኤልክትሮንክስ ጥገና ሎት 6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት ሎት 7 የህትመት ስራ ሎት/8 መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ ሎት10 የፈርኒቸር ጥገና ሎት11 ቋሚ እቃዎች ሎት /12 የጉልበት ስራ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንድሳተፉ ይጋብዛል።
2. የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች በመስኩ ህጋዊ የታደስ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና ቨት ሰርትፍኬት ኮፒዉን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችል ይሆናል። ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል።
3. ተጫራቾች በቅዲሚያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) የሚጫረቱበት ሎት1/ የደንብ ልብሶች ግዢ ብር 20,000 ሎት/2 የጽዳት እቃዎች 20,000 ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች 25,000 ሎት/4 ልዩ ልዩ እቃዎች 19,500 ሎት/5 የኤልክትሮንክስ ጥገና 2,000 ( ሎት/6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት 15,000 ሎት 7 የህትመት ስራ 5,000 ሎት/8 የመስተንግዶ አገልግሎት 2,500 ሎት/9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ 12,000 ሎት/10 የፈርኒቸር ጥገና 2,400 ሎት/11 ቋሚ እቃች 5,000 ሎት 12 /የጉልበት ስራ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. የመጫረቻ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት እና ለየብቻ በማሸግ ከጨረታዉ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/07 ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ይከፈታል ይህ ቀን የበዓል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
6. በግዥ አዋጁ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛልማትልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ስለመደራጀታቸው የሚገልፅ ከአደራጃቸው ተቋም በጽ/ቤቱ ሃላፊ የተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
7. የአንዱ ዋጋ የማይለወጥ በመሆኑ ተጫራቾች በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም የዕቃዉ ጥራትና ዋጋ ከግምት በማስገባት እንዲሞሉ እገልጻለን።
8. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢው ወረዳው እስቶር (ዕቃ ግምጃ ቤት) ድረስ አምጥቶ የሚስረክብ በመሆነን ከግንዛቤ ውስጥ እንድታስገቡ፤
9. የዕቃውን 20 ፕርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ መ/ቤቱ የሚችል መሆኑን እና ጠቅላላ ዋጋውን 25 ፐርሰንት ለ6ወር ድረስ ጨምሮ ሊያዝ የሚችል መሆኑን።
10. ተጫራቹ ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ሳምፕል ናሙና) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡– የጉልበት ለሚወዳደሩት በሰራ እድል ፈጠራ የተደራጁ ቢሆን ደብዳቤ እና የቲን ቁጥር ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ፡– ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/07 ቤቴል እሳት አደጋ ፊት ለፊት በ40 ሜትሩ መንገድ በኩል ነው
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 011 369 6634 ይደውሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት