ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 5 ያገለገሉና በጥሩ ይዘት የሚገኙ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 5 ያገለገሉና በጥሩ ይዘት የሚገኙ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Aug 09, 2026)

ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ ማስታወቂያ

(በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ)

ዘመን ባንክ .. በቁጥር 5 ያገለገሉና በጥሩ ይዘት የሚገኙ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ደንቦች፡

1. ሞተር ሳይክሎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከነሐሴ 4 ቀን 2018 . እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2018 . ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሞተር ሳይክሎቹንጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ /ቤትአካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-58-25/011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 12 ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፣

2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አሰተዳደርና ሎጂሰቲክሰ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመረጡትን ሞተር ሳይክል/ሎች ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2018 . ከቀኑ 1100 ድረስ በባንኩ ዋና /ቤት ህንጻ 12 ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው ነሐሴ 14 ቀን 2018 . ከቀኑ 1100 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ነሐሴ 15 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 330 ላይ በባንኩ ዋና /ቤት ህንጻ 19 ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።

6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት። ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤

7. ባንኩ ንብረቱን በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

8. ከስም ዝውውር፤ እንዲሁም ሞተሮቹን ከማስተካከል፤ ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል።

9. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል።

10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ .

Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *