የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Aug 12, 2026)

ያገለገሉንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤

በአዲስ አበባ ቦሌ ክሬሸር ሳይት በሚገኘው የዕቃ ግምጃ ቤት ተከማችቶ የሚገኙ ዝርዝራቸው በመጫረቻ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ንብረቶች የኮንስትራክሽን መገልገያ ዕቃዎች፣ ሚክሰር፣ ኮምፓክተር፣ ኮምፕረሰር፣ ቫይብሬተር፣ ተሸከርካሪ፣ ማሽነሪ ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፣

የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተመለከተው የኩባንያው አድራሻ በመቅረብ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና መጫረት ይቻላል።

የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች፣ ንብረቱ በሚገኝበት በአዲስ አበባ ቦሌ ክሬሸር /ከሰፊራ መስጊድ ወደ አይ.ሲ.ቲ በሚወስደው መንገድ በመገኘት በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በመገኘት ዕቃውን መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን በ18/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋው 20% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ ከፍሉ በቀጣዩ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን ንብረት አውጥቶ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያሸነፈበትን ዕቃ ካላወጣ ግን ኩባንያው ኃላፊነቱን አይወስድም።
“ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።”

የንኮማድ ኮንስትራክሸን ኃ/የተ/የግል ማህበር
አድራሻ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ
ዕቃና አገልግሎት ግዥ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107
ስልክ ቁጥር 0115523022


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *