Addis Zemen (Aug 18, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን
- ሎት 1 ፡– የጽህፈት መሳሪያዎች እና የፎቶ ኮፒ የፕሪንተር ቀለሞች ለመግዛት
- ሎት 2 ፡– የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት
- ሎት 3 ፡ የጽዳት ዕቃዎች ለመግዛት፣
- ሎት 4 ፡– ህትመትና ቦርድ ማስታወቂያ በውል ለማሠራት
- ሎት 5 ፡– የፕሮዳክሽን ሥራ ለማሠራት
- ሎት 6 ፡– የኤሌትሪክ መኪና ኪራይ ለ2019 በጀት ዓመት ለመከራየት
- ሎት 7 ፡– የግንባታ፣የኤሌትሪክ እና የቧንቧ ዕቃዎች ለመግዛት
- ሎት 8 ፡– የምግብ የለስላሳ መጠጦች የአንድ ዓመት በውል ለመግዛት
- ሎት 9 ፡– የእንስሳት ቀለብ የሚሆን ሥጋ በውል ለመግዛት
- ሎት 10 ፡– የአትክልትና ፍራፍሬ አይነት ለመግዛት
- ሎት 11 ፡– የእንስሳት ሕክምና ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች ለመግዛት
- ሎት 12 ፡– የግብርና ግብዓቶች ዕቃዎች ለመግዛት
- ሎት 13 ፡– የውሃ ቦቴ በውል ለመከራየት
- ሎት 14 ፡– የጽዳት ድርጅቶችን አስገብቶ በውል ለማሠራት
- ሎት 15 ፡– የፋውንቴንና ኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን በውል በማሰር ለማሠራት
- ሎት 16 ፡– የግንባታ ሥራዎች እና ጥገናዎች ለማሠራት
- ሎት 17 –የኮምፒተር፣ፕሪንተር እና የፎቶኮፒ ጥገና ሥራ ለአንድ ዓመት ውል በማስር ለማሠራት
- ሎት 18 ፡– የሳር ማጨጃ ማሽን ለመግዛት
- ሎት 19 ፡– ኮምፒተር ፣ ፕሪንተር እና ላፕቶፕ ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራጮች ተጋብዘዋል።
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት በታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (clearance) ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ሎቶች 500,00.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ሕንጻ ላይ ሦስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን በኋላ ባለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ሕንጻ ላይ ሰባተኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
6. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
7. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፣
8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር 0915 862 636 / 0923 389 872 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን