የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በከተማ ውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር የሚተከል ምልክትና ማመላከቻ ሳህንና የሚቆመውን ብረት የከተማውን ደረጃ የሚመጥነውን ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በከተማ ውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር የሚተከል ምልክትና ማመላከቻ ሳህንና የሚቆመውን ብረት የከተማውን ደረጃ የሚመጥነውን ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በከተማ ውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር የሚተከል ምልክትና ማመላከቻ ሳህንና የሚቆመውን ብረት የከተማውን ደረጃ የሚመጥነውን ለማሰራት ስለተፈለገ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል አጫርቶ ማሰራትን ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት:-

1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች –

2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው በጨረታው እንዲሳተፉ የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ – ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ / የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።

7. በቂ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት እንደምትችሉ እናረጋግጣለን፣

8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046-212-1334

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *