በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 31, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019

በኮ/ቀ/ ክ/ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ209 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት1 የደንብ ልብስ
  • ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3 የህትመት ስራ
  • ሎት 4 የህከምና እቃዎች
  • ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች
  • ሎት 6. የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 7 የት/ት መሳሪያዎች መጽሀፍት መግዣ
  • ሎት 8. ፕላት ማሽነሪ
  • ሎት.9. የተገጣጣሚ እና ቁሳቁስ መግዣ
  • ሎት 10 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • 11የተገጣጣሚ እና ቁሳቁስ ጥገና 
  • ሎት 13የጉልበት እና የትራንስፖርት
  • ሎት 15 ፣ልዩ ልዩ ከፍያዎች

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈረት የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. ተጫራቾች ከስራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፤

2.ት/ቤቱ በሚሽጠው ሰነድ ላይ የሚፈለግባችሁን በመሙላትእና በፖስታ በማሸግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር/መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታዎች ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ /cpo) የብር መጠን በየሎት ለእያንዳንዱ ሎት1. 21,000 ሎት 2. 25,000 ሎት 3. 2,000 ሎት 4 1,000 ሎት.5. 17,000 ሎት.6. 20,000 ሎት.7 15,000 ሎት 8. 15,000 ሎት.9, 15,000 10. 1,500 ሎት 11 .10,000 ሎት 13. 6,000 ሎት 15 3,000 ማሲያዝ አለባቸው፡፡

5. በጥቃቅን አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ካደራጀው ተቋም በኃላፊ ብቻ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ሲኖረው በስራ ሂደት የሚፈረም ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበት የእቃ ናሙና በተመረጡ ሎት እና ሌሎች ናሙና ማቅረቢያ ዘዴ ማቅረብ አለበት፡፡

7. የኤሌክትሮኒስ ጥገና እና የቁሳቁስ ጥገና ላይ አሸናፊ የሚሆኑት ውላችን የአንድ ዓመት መሆኑ ይታወቅ፡፡

8.ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በግዥ ከፍል ይከፈታል፡፡

9. ተጨራቾች ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና አሁድ /የበዓላት ቀን /የሚውል ከሆነ ቀኑን አሳልፈን የምንከፍት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡

10.መስ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል /በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ ካራ ቆሬ ወደ ረጲ መደሃኒያለም ቤተክርስቲያን መሄጃ ፖሊስ ጣቢያውን አለፍ ብሎ የሚገኘው ት/ቤት ተጨማሪ መረጃ፡- 011 369 5428 /011 369 5841/

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትነባሩ ህንጻ 1ኛ
ወለል ግዥ ቢሮ ቁጥር 9፡
በኮ/ቀ/ ክ/ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት