Be'kur (Sep 07, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ደንምቢያ ጤና ጥበቃ ስር የሚገኘው የአይምባ ጤና ጣቢያ የAPTS ሸልፍ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ጥሩ ስነምግባር ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አይምባ ጤና ጣቢያ ግዥ/ፋ/አስ/ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጳጉሜ 02/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 12/2019 ዓ.ም በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጉ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ መገኘት ካልቻሉ ጨረታው ሰዓቱን ጠብቆ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከፖስታውና ከእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅታችሁ ማህተም በማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዣ የሚሆን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከካርድ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ አይምባ ጤና ጣቢያ ፋን/አስተ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 08 07 09 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአይምባ ጤና ጣቢያ