በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶችን ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎችን የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶችን ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎችን የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 08, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጎተራ ማሳ///02/2019 .

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ /ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን እቃዎች እና አገልግሎቶችን 2019 . በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ብቁ ከሆኑ ተወዳዳሪዎች ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

  • ሎት 1. ጨርቃ ጨርቅ፣ ቆዳ ጫማ ውጤቶችና ተዛማጅ (ደንብ ልብስ)
  • ሎት 2. የአላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3. የህትመትና ተያያዥ ስራዎች
  • ሎት 4. መድኃኒት እና የህክምና ማሽን ሪኤጀንቶች
  • ሎት 5. የቢሮ ፅዳት መገልገያ እቃዎች
  • ሎት 6. የቢሮ ቋሚ የእንጨት ውጤቶች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 7. የሰራተኞች ልብስ ስፌት አገልግሎት
  • ሎት 8. የቢሮ ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
  • ሎት 9. ለተሽከርካሪዎች እና ለሌሎች መጓጓዣዎች
  • ሎት 10. ለግብርና፣ ለደንና ለባህር ግብዓቶች
  • ሎት 11. ለህንጻ ፣ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና)
  • ሎት 12. የንግድ ቤት ጨረታ
  • ሎት 13. ልዩ ልዩ
  • ሎት 14. የመጫንና የማውረድ አገልግሎት (ጉልበት ሰራተኛ
  • ሎት 15. አነስተኛ ሽፍን የጭነት መኪና አገልግሎት

በዚህም መሰረት በታች የተዘረዘሩትን የቴክኒክ መመዘኛ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል።

1. ከሎት አንድ እስከ ሎት 12 ያሉት በዘርፉ የተሰማሩ 2018/2019. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት (egp) ፣የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣የታደሰ ግብር ከፋይነት ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ያለው ማቅረብ የሚችል።

2. ከሎት 13 እስከ 15 ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አይጠበቅባቸውም

3. በሎት 14 እና 15 ለአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የማይገደዱ ሲሆን በሎት 14 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ፣ሎት 15 ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ 3 ወገን ኢንሹራንስ፣ ሊብሬ ኮፒ ፣መኪናው ለመድኃኒት ጭነት አመቺ የሆነ ሽፍን የነዳጅና ሌላ ፍጆታዎች በራሱ መሸፈን የሚችል፣

4. ለሎት 12 ተጫራቾች ከሚጠቀሰው የመነሻ ዋጋ በላይ የሚያቀርቡትን የወር ኪራይ ዋጋ በግልጽ መግለጽ አለባቸው:: የታወቀ መታወቂያ ወይም ህጋዊ የድርጅት ሰነድ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያውን መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት 230-630 ከሰዓት 730-1130 ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ ሎት ክፍያ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 409 በመፈጸም የጨረታ ሰነድ ከግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 410 መውሰድ አለባቸው፡፡አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው 10 (አስር ቀን) የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ 10ኛው ቀን 1100 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም የጨረታውን መክፈቻ የሚያስተጓጉል አይሆንም።

7. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋጋጠ CPO ለሎት 1 ብር 10,000.00 ሎት 2 ብር 13,000.69 ሎት 3 ብር 5,000.00፣ሎት4 ብር 50,000.00፣ሎት 5 ብር 17062.00፣ሎት 6.ብር 52478.37፣ሎት7.ብር 10,000.00፣ሎት8 ብር 7,696.00 ሎት 9.ብር 6,000.00 ለሎት 10.ብር 4,000.00,ሎት 11.ብር 67,322.45፣ለሎት 12.ብር 5000.00 ለሎት 13 ብር 5,000.00, ሎት 14.ብር 5,000.00 ሎት 15 ብር 5000.00 በጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ በማሰራት ከሚያቀርቡት ቴክኒካል መረጃ ጋር አሲዘው ይጠበቅባቸዋል፡ በተመሳሳይ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራ ከሆኑ ካደራጃቸው /ቤት በጤና ጣቢያው ስም የድጋፍ ደብዳቤ በማስጻፍ ከሚያቀርቡት ቴክኒካል መረጃ ጋር አሲዘው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

8. ለህንጻ፣ ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ከደረጃ አምስት በላይ መሆን አለበት።

9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስም፤ ማህተም፣ፊርማ በማድረግ የጨረታውን አይነት ሎት በግልጽ በመግለጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለህክምና ቋሚ እቃ ተወዳዳሪዎች material specification በተጨማሪ ለብቻ በፖስታ ታሽጎ ፊርማ፣ ማህተም፣ ሎቱ ተገልጾ መቅረብ አለበት፡፡ በሁሉም ሎቶች ላይ ዋጋ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም የእቃ specification በራስ ማስተካከል በዛ እቃ ወይም አገልግሎት ላይ ተወዳዳሪ አያደርግም።

10. ተጫራቾች የእቃ ናሙና እና በፎቶ ለተጠየቁባቸው እቃዎች ወይም አገልግሎት ናሙናውን ቀድመው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በዝርዝር አስመዝግበው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በፎቶ ናሙና ለተጠየቀባው እቃዎች ውል ከመገባቱ በፊት ጤና ጣቢያው በሚያዘው መሰረት አንድ የተሰራ ወይም የተዘጋጀ ናሙና በማቅረብ አስፈላጊ እየታ ተደርጎ ጥራቱ ከተረጋገጠ ውል ፈርሞ ቀሪ እቃ ማቅረብ አለበት፡፡ የደንብ ልብስ ስፌት 2018. መልካም አፈጻጸም ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅበታል።

11. ጤና ጣቢያው በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በጨረታ በግዥ ትዛዝ ላይ 20% የመጨመር እና 20% የመቀነስ መብት አለው፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ማሸነፉን ከተገለጸለት በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ከጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ በጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ ስም አሰርቶ ማስያዝ አለባቸው።

12. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ /ጣቢያው አድራሻ መጋዘን አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

12. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።

13. /ጣቢያው ለሚፈጽመው ግዥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለ መረጃ

ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር 300 ሜትር ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ፌት ፊት

ተጨማሪ ማብራሪያ፡ስልክ ቁጥር 0114 700 844 መጠየቅ ይችላሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ /ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ