Addis Zemen (Sep 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 3 የፅዳት ዕቃ፣
- ሎት 4፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
- ሎት 5 የህትመት ዕቃ
- ሎት 6፣ የመስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 7 የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር ጥገናዎች
- ሎት 8 የተለያዩ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 9 የድንኳንና ዲኮር መሰል ዕቃዎች ኪራይ
- ሎት 10 የግብርና ዕቃዎች
- ሎት 11 የመኪና ጎማ
- ሎት 12 የመኪና ኪራይ የሕዝብ ማመላለሻ
- ሎት 13 የመኪና ኪራይ የጭነት እስከ 30 ኩንታል
- ሎት 14 የፈርኒቸር ዕቃዎች
- ሎት 15 የቀን ሰራተኛ ጉልበት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማሰረጃ፣ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ስም ምዝገባ/ምስክር ወረቀት/፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በንግድ ሥራ ፍቃድ በጀርባው ያለውን የሥራ ዘርፍ የተገለፀበትን ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ እና የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ
4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት ሶስተኛ (3)” ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የቀን ሰራተኛ ጉልበት ውጭ ለሁሉም ሎት ሀያ ሺህ (20,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በየአንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በየአንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ዋጋ ማቅረቢያ ሲያቀርቡ ኦርጅናል ደረጃውን የጠበቀና ናሙናውን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት ለግዥ ክፍል ማስረከብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች ያሸነፉአቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን በቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
9. ጨረታው የሚዘጋበት በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ላይ ይሆናል።
10. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ለ አሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡
11. ናሙና የሚያስፈልጉ እቃዎችን በተባለበት ቀን ውስጥ ማስረከብ አለባቹ
12. ክፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ለ ፋ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና የቀረበው ዕቃ በ ናሙና መሰረት በጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
13. በጨረታ ሰነዱ ላይ የዋጋ ስርዝ ድልዝ እና ጽ/ቤቱ የሠጠውን እስፔስፊኬሽን መሰረዝ የለበትም፡፡
14. የጨረታ ማስረከቢያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ ለምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ/ዘርፍ/ የሚገልጽ ደብዳቤ መቅረብ አለበት።
15. ዋስትና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አሸናፊው ለ1ዓመት የሚቆይ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
16. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
17. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ ትክክል መሙላት ይኖርባችኋል።
18. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር +251118668057 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት
- ከአያት ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ብርሀን ባንክ ያስበት ሕንጻ 3ኛ ፎቅ አካባቢው ልዩ ቦታ ክብር ደመና።
ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት