የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ቤ/ቤት በ ቀን 06/01/2019 ዓ/ም እና 09/01/2019 በግልጽ በሀገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ የቅድሚያ አካውንት በተጫራቾች ስም የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነዱ ባለበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክላችሁ በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማግኘት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሚያሟላ ጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የዕቃዎችን ሰምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ዕ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ዕ/ቤት፡እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣላችሁ የምትፈልጉት የአቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ዕ/ቤት እንዲመጣላችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች

1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ተጫራቾች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቀስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፡ በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥርና አመራረጅ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጠዋት 3:45 09/01/2019 ባሉት ቀናት ለአገር አቀፍ ጨረታ እስከ ቀን 06/01/2019 ዓ/ም እና እስከ ረፋዱ 5:00 የሰነደውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ዕ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ዕ/ቤት ስም በተከፈተ ታክስ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባለበት በቴሌግራም እንዲላክለት ማድረግ ይችላሉ።

3.  ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሀገር አቀፍ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አረጋግጠው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ዕ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.  ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናቶች (እስኬጁል) መሠረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

የጨረታ ቦታ

የጨረታ ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

ጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

ቃሊቲ ጉምሩክ

ግልጽ እና ሃራጅ

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ መኪና መለዋወጫ፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ተሸከርካሪ፣ የሞባይል ቀፎ አክሰሰሪ፣ ምግብ ነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣

ለግልፅ ጨረታ እስከ 06/01/19 አርብ እና 09/01/2019 ቅዳሜ ጠዋት 3:45 እና ለሀራጅ  ጨረታ እስከ 4:45

ለግልፅ ጨረታ 06/01/19 እና 09/01/2019 ጠዋት 3:45 እና ለሀራጅ ጨረታ እስከ 5:00

5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዘቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (C.P.O) ከማሸነፉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርባቸዋል።

8. ከላይ በቁጥር7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኮሚሽኑ የገቢ የተደረገ እና ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት