Addis Zemen (Sep 12, 2026)
እርሻ መሳሪያዎች ፤ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ኢማ መነሻ ግምታቸው ብር 12,355,256.2 /አስራ ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ስድስት ብር ከ12/100/ የሆኑ እርሻ መሳሪያዎች፣ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተጫራቾች የእርሻ መሳሪያዎች ፤ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) ኩባንያው በሚገኝበት አዲሰ አበባ ቦሌ ጃፓን ገነተ ልማት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 755 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ከሶስተኛው ቀን ጀምሮ ኩባንያው በሚገኝበት አዲስ አበባ ቦሌ ጃፓን ገነተ ልማት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 755 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡05 ይከፈታል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ በቅድሚያ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በገንዘብ ከፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለበት።
አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
የስም ዝውውር እና ሌሎች ተያያዥ በመንግስት የሚጠየቁ ወጪዎች ጨረታውን ባሸነፈው ተጫራች በገዥው የሚሸፈኑ ናቸው።
የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት የገዛበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
ገዢው በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% _ /አስራ አምስት በመቶ መክፈል ይጠበቅበታል።
ተጨማሪ መረጃ 0912 23 70 91 ፤ ዐ915 66 66 66 ደውሎ ማግኝት ይቻላል።
ተጫራቾች እርሻ መሳሪያዎች የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎችን መመልከት ከፈለጉ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ.ማ