Addis Zemen (Sep 11, 2026)
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-08/2019
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት
- የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች
- አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣
- የኤሌክትሪክ/ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
- የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
- ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች
- የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች
በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በመሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች (ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ክፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡ዐዐ ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳቦችና ቀረጥ ተመላሽ አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት https://t.me/hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5%(አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.PO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የጨረታ ዋስትና( CPO) መጠን ለእያንዳንዱ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤፤
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ቅጥር ግቢ ውስጥ 405 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚኖር ሲሆን ግን ወታታት ተርታ በኃላ የሀራጅ ጨረታ ተሳታፊዎች ምዝገባ ተጀግሮ እንደተጠናቀቀ ይጀምራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልጽ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ አንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች የጨረታው መሳተፍ አይችሉም። በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ የጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አልያም አይነበብልን ማለት አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ /ቤቱ የጨረታዉን ዉጤት እስከሚያሳዉቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም:: በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5( አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ግቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046-212-5396/ 046-212 6595
ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት