Reporter (Sep 13, 2026)
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ, ብ/ባ/ፕ/የ/ማ/ሎ-04/19
ብርሃን ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት
1.ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሜክስኮ ዲ–አፍሪክ ሆቴል ጀርባ በሚገኘዉ የብርሀን ባንክ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
2.ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ሕንፃ 2 ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ፣ እንዲሁም ሰንጋተራ ከሚገኘዉ ከባንኩ ሰንጋተራ ቅርንጫፍ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለጸዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ሞተር ሳይክል የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ሞተር ሳይክል በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ሞተር ሳይክሎች አንድ እና ከዛ በላይ በተናጠል ተወዳድረዉ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ ለእያንዳንዱ ሞተር ሳይክል በተናጠል በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት፣ የጨረታ ማስታወቂያዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ኤንቬሎፕ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታዉ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል::
7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸዉን ሞተር ሳይክል/ሞተር ሳይክሎች፣ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለጸላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
8. የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈበት ሞተር ሳይክል/ሞተር ሳይክሎች ከስም ማዛወሪያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
9. ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ።
10. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116631729 /0998454424 / 0998411523 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ።