Addis Zemen (Sep 15, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2019
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ያገለገሉ የሞተርሳይክሎች እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፤ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤የመገናኛ መሳሪያዎች፣ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፤ ነዳጅ፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች ፤የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
2. ተጫራቾች የግልጽ እና ሐራጅ ጨረታ ሰነድ በቴሌግራም አካውንት የሚላክላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማህተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁ.ር 16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ፣ ሌሎች ከላይ የተገለጹ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ. ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
5.ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡
6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሦስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 444 1415 / 046 444 1564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት