በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ገቢዎች ሚኒስቴር የጫማ ማምረቻ ማሽኖች፣ የአንፖል ማምረቻ ማሽኖች፣ የልብስ መስፊያ ማሽኖች፣ ጄነሬተር፣ የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችንና የሞተር ሳይክሎችን ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ገቢዎች ሚኒስቴር የጫማ ማምረቻ ማሽኖች፣ የአንፖል ማምረቻ ማሽኖች፣ የልብስ መስፊያ ማሽኖች፣ ጄነሬተር፣ የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችንና የሞተር ሳይክሎችን ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 15, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን

  • የጫማ ማምረቻ ማሽኖች፤
  • የአንፖል ማምረቻ ማሽኖች የልብስ መስፊያ ማሽኖች፣
  •  የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችንና የሞተር ሳይክሎችን ለመሸጥ

የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ 01/2019 የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከሊያንችን ፕላስቲክ ፕሮዳክሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የጫማ ፋብሪካ የተያዘ የጫማ መምረቻ ማሽን ፣ ከኤቢሲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የአምፖል ማምረቻ ማሽኖች፣ ከኤሊኤላ ጋርመንትና ጨርቃ ጨርቅ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ የልብስ ስፌት ማሽን /ሴንጀር የተለያየ ብትን ጨርቅና የተሰፋ ቲሸርት ጃኬት እንዲሁም ጄነሬተር፤ ከእሺ ፈጣን መልዕክት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከአረብ _ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር፤ ከምቾት ዳይፕር ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን እና የሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም።

  1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የገልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-600 ሰዓት ህንፃ “መ“ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ አንድ አስረኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Ministry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ። 

    ተ.ቁ

    የመ/ቤቱ ስም

    ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

    የንብረቶቹ

    መመልክቻ ቀን

    የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

    1

    ገቢዎች ሚኒስቴር

    የጫማ ማምረቻ ማሽኖች የአንፖል : ማምረቻ ማሽኖች የልብስ ስፌት ማሽን የተለያየ ብትን ጨርቆች፣ ጃኬት እንዲሁም ጀነሬተር እና የለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎች

    ማስታወቂያው በጋዜጣ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት

     

    ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተግቶ በዚያን ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

     

  5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለቤት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  6. የግልፅ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
  7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር አንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡
  8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ -ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት /ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ያቀርባል፡፡
  11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮ 011617-84-90 ኮድ 2044 (2045) (2046) የውስጥ

መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዊብሳይት www.MOR.GOV.et መመልከት ይቻላል፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር