Reporter (Sep 20, 2026)
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና መለዋወጫዎች
የጨረታ ማስታወቂያ
አንጋፋ የአውቶሞቲቭ ኩባንያ ኦርቢስ የንግድ እና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ. በኢትዮጵያ ስመጥር የሆኑትን የመርሰዲስ ቤንዝ እና ሬኖልት ተሸከርካሪዎች ብቸኛ አስመጪ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም ኩባንያችን በመጋዘናችን የቆዩ የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን (የመርሰዲስ የቦሽ፣የሬኖልት፣ቦማግ) እና የኮሚኒዩኬሽን መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች (የሞቶሮላ) እንዲሁም መርሰዲስ ቤንዝ፣ ሬኖልት ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራች የሆናችሁ ሜክሲኮ በሚገኘው መ/ቤታችን ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት የመኪኖቹን እና የመለዋወጫዎቹን ዓይነት እና ዝርዝር ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1.ተጫራቾች ንብረቶቹን ከመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 02፡00-10፡30 ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ዝቅ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
2.ጨረታው አርብ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ተዘግቶ በማግስቱ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋት 04:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
3.ለጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
4.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
5.በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
6.ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7.ለበለጠ መረጃ መለዋወጫዎችን በተመለከተ፡
በስልክ ቁጥር፦ 0913773127 እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 0974656420 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
ኦርቢስ ንግድና ቴክኒክ ማዕከል አ.ማ
ስልክ፡ 115516211/115510078