የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የጽድ ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የጽድ ዛፍ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 19, 2026)

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በዞኑ በአ/ምንጭ ዙሪያ ወረዳ እና በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ መሀል በደገና ቀበሌ የጉጫ ኮንፓርትመንት ሰው ሰራሽ ደን 8.09 ሄክታር ላይ ያረፈ የደረሰ የጽድ ዛፍ በቁጥር 3398 በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ያላቸው ፣
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው ፣
  3. የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ያላቸው ፤
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይ መሆናቸው ማስረጃ ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የደኑን መገኛ ቦታ በራሱ ወጪ አይቶ የአንዱን ጽድ ነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች ደኑን ለማንሣት አስፈላጊውን የሰው ኃይልና መሣሪያዎችን በራሣቸው ማቅረብ የሚችሉ፣
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር 300.00/ ሦስት መቶ ብር/ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000038613263 በማስገ ባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኙን በማሳየት ከጋሞ ዞን ፋይ ናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BiD security) 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በዋናው የሕጋዊነት ሰነድ እንቬሎፕ ውስጥ አስገ ብተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
  12.  የጨረታ መክፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠ በቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር- 046-881-3338 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጋሞ ዞን
ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
አ/ምንጭ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *