Addis Zemen (Oct 23, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 04/2019 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
ዘርፍ |
የጨረታው ዓይነት |
ዕቃው ያለበት ቦታ |
|
1 |
የፅዳት ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
2 |
ኮስሞቲክስ |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
3 |
ምግብ ነክ |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
4 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
5 |
ኮስሞቲክስ |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
6 |
ጫማ |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
7 |
የእጅ ሰዓቶች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
8 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
9 |
ፓኪንግ ማሽን |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
|
10 |
መለዋወጫዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ የመንግሥት መጋዘን |
በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡–
1.በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃ ድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም። በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00-5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ የመንግሥት ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው መለዋወጫዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ ኮስሞቲክስ(ምድብ 01) ብር 50,000(ሀምሳ ሺ ብር፣ ኮስሞቲክስ (ምድብ02) ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር)፤ ጫማ (ምድብ01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፤ጫማ (ምድብ 02) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር)፤ ጫማ (ምድብ 03) ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፤ ኤሌክትሮኒክስ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፤ የእጅ ሰዓቶች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፤ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና(CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንከ አሠርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 19/02/2019 |
20/02/2019 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል |
|
2 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት |
ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 19/02/2019 |
20/02/2019 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
5. ጨረታው መክፈቻ ቦታ፡– በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጠጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።
11. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡– 033 240 1510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት