በደ/ኢት/ያ ክልል በወላይታ ዞን አፋ ወረዳ ፈፋ/ስና ፕ/ል/ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል የተለያዩ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደ/ኢት/ያ ክልል በወላይታ ዞን አፋ ወረዳ ፈፋ/ስና ፕ/ል/ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል የተለያዩ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 29, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በ2019 በጀት ዓመት በደ/ኢት/ያ ክልል በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ፈፋ/ስና ፕ/ል/ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች የሚውል በአራት ሎት የተጠቀሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መሰፈርት ሊወዳድር ይችላል።

  • ሎት 1. አላቂና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት 2. የፋብሪካ ውጤቶች
  • ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 4. የአስተዳደር ደንብ ልብስ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የተጫራቾች መመሪያ

1. የታደስ የዘርፉን ንግድ ሥራ ቲን ከርድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምሰክር ወረቀት፤ እና ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡

3. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻው ቀን ሙሉ ስም ከነአያት፤ አድራሻ፤ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም በትክክል ተደርጎ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ወስጥ መክተት ይኖርበታል፡፡

4. ፖስታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡

5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000/አስር ሺህ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. መ/ቤቱ ከአሽናፊ ተጫራች ጋር ውል ይገባል፡፡

7. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታዉቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛዉ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በኦፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት እዝ ኦፊስሮች ቢሮ ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ሰንበት ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች በገዛ ፈቃድ በጨረታ ቦታ ያለመገኘት የጨረታዉን ሃደት አያስተጓጉልም፡፡

8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለዉ መሆን የለበትም፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታዎቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኦፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት እዝ ኦፊስሮች ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ያሸነፈ ተጫራች በደብዳቤ ከተገለፀ በ3 ቀናት ውስጥ የውል ማሰከበሪያ/Performance Bond/ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 10% ብቻ በማቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል፡፡

11. የጨረታ ማስከበሪያ አሽናፊ ተጫራች እንደታወቀና ውል ከተፈራረመ በኃላ ለተሸናፊ ተጫራች ተመላሽ ይደረጋል፡፡

12. አሸናፊ ተጫራች ዕቃውን ኦፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ግቢ አድርሶ ያስረክባል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ጋገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ የቢሮ ስልክ +251 464 690 420 or 0928 720 977

በደ/ኢት/ያ ክልል በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ፈፋ/ስና ፕ/ል/ ጽ/ቤት