የመኪና እና ያገለገሉ ንብረቶች (ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ ፋክስ ማሽን፣ ተሽከርካሪ ወንበር….) የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የመኪና እና ያገለገሉ ንብረቶች (ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ ፋክስ ማሽን፣ ተሽከርካሪ ወንበር….) የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Nov 03, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ዘይነብ ያህያ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ሙላታ ኑር ሁሴን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 106960 በ5/2/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/114322 በ30/03/2017 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/114322 በ08/10/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ. ኮድ 2-37126 አ.አ ሞዴል 504SR Peejo ( ፔጆ ) ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 157,440 (አንድ መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ አርባ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

2ኛ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 073/07 ውስጥ የሚገኙ ፍ/ያረፈባቸው ያገለገሉ ንብረቶች (ላፕቶፕ ፎቶ ኮፒ ፋክስ ማሽን ተሽከርካሪ ወንበር….) የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 87,584 (ሰማንያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ አራት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውስድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት