የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ እና አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 4. ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ፈርኒቸር)፣
  • ሎት 5. ደንብ ልብሶች፣
  • ሎት 6. የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች፣
  • ሎት 7. የእንሰሳት መድሀኒት፣ የመገልገያ መሳሪያዎች እና ኬሚካልና የላብራቶሪ እቃዎች፣
  •  ሎት 8. የእንስሳት መኖ፣
  • ሎት 9. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች እንዲሁም
  •  ሎት 10. የስፖርት ትጥቅ እና የስፖርት መገልገያ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም እቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ ስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከላይ በዝርዝር ከሎት 1. እስከ ሎት 10. ድረስ የተቀመጡትን እቃዎች በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ ማስፈተሸ ይኖርባቸዋል፡፡
  4.  ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት ቡኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ስምና ፊርማ፣ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገጹ ማህተም ማድረግ እና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6.  ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን እንዲሁም ቫት ዊዝሆልድን 7.5 በመቶ ታሳቢ ተደርጎ መሞላት አለበት፡፡
  7. ውድድሩ በድምር ዋጋ /ሎት/ መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  8.  ጨረታ ሰነዶችን ለያንዳንዳቸው ሎቶች ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜው እሁድ ቅዳሜ ወይም የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የሚከፈት ይሆናል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 144/2018 መሰረት ተገዥ የመሆን (የመቀበል) ግዴታ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
    • ለሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር)፣
    • ለሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር)፣
    • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር)፣
    • ሎት 4. ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ፈርኒቸር) ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሽህ ብር)፣
    •  ሎት 5. ደንብ ልብሶች ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር)፣
    • ሎት 6. የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች ብር 7,000 (ሰባት ሽህ ብር)፣
    • ሎት 7. የእንሰሳት መድሀኒት፣ የመገልገያ መሳሪያዎች ፣ ኬሚካልና የላብራቶሪ እቃዎች ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሽህ ብር) እና
    • ሎት 8. የእንሰሳት መኖ ብር 4,000 (አራት ሽህ ብር)፣
    • ሎት 9. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ብር 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር)
    •  ሎት 10. የስፖርት ትጥቅ እና የስፖርት መገልገያ መሳሪያዎች፣ ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት
      ይኖርባቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ ለሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ስለሆነም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡

13. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ እና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የተሳሳተ (ስርዝ ድልዝ) የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል በህግም ያስቀጣል፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 79 04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

16. ከየሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

17. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች መ/ቤቱ የሚያስቀምጣቸውን ናሙናዎች በማየት ዋጋ ሊሞሉ ይገባል፡፡

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ