Be'kur (Nov 09, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3. የቢሮ መገልገያ እቃዎች ሎት 4. የጽዳት እቃ፣ ሎት 5. የፋብሪካ ማቴሪያል፣ ሎት 6. ደንብ ልብስ፣ ሎት 7. ፈርኒቸር፣ ሎት 8. ህትመት፣ ሎት 9. የመኪና ስፔርፓርት እቃዎችን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና 2018 ዓ.ም የሥራ ግብር ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ያጠናቀቀ እና በ2019 የሚጠበቅበትን ከፍለው ያጠናቀቁ መሆን ይኖርበታል፡፡ ግብር ለመክፈሉ ከገቢዎች ጽ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2 በመቶ የጨረታ ሳጥኑን ከመከፈቱ ቀድሞ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ያሸነፉትን የእቃ ዋጋ 10 በመቶ ወዲያዉኑ በማስያዝ ዉል በመዉሰድ የተጠየቀዉን እቃ ጥራት ጠብቆ ሊያቀርቡ ይገባል፡፡
4. ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ዉል የማይወሰድ ወይም ዉል ከወሰደ በኋላ እቃዉን የማያቀርብ ተጫራች ቢያጋጥም መ/ቤቱ ለዉል ማስከበሪያ የያዘዉን ገንዘብ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ አንድ ዓመት ለሚደረስ ጊዜ በጨረታ እንዳይሳተፍ የማገድ ስልጣኑን ለመጠቀም ይገደዳል፡፡
5. ማንኛዉም ተጫራች የማወዳደሪያ ዋጋ ሲሞላ ሁለት ኦርጅናል በሁለት ፓስታ ታሽጎ ማስገባት ከጨረታዉ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ሳጥኑ መግባት ያለበት ኦርጅልናል ኮፒ ጋር ሆኖ በሁለት ፖስታ ታሽጎ ከፖስታዉ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተጽፎ ከሳጥኑ ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ማንኛዉም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን የማይመለስ 1 ኮፒ የግብር ከፋይ ምዝገባ ኮፒ፣ ቫት (ቲኦቲ) የምስክር ወረቀት የማይመለስ 1 ኮፒ የግብር ክሊራንስ ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ማንኛዉም ተጫራች ለሚያቀርበዉ እቃ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
9. ማንኛዉም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን የጨረታ ሰነዱን በ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በመ/ሰ/ከ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 210 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
10. ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሲሆን ታሽጎ ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
11. የሚቀርበዉን እቃ በተጠየቀዉ መሰረት መሆን ይጠበቅበታል፡፡
12. የሚቀርበዉ እቃ ጥራቱን የጠበቀ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
13. በጨረታዉ ያሸነፈዉ ግለሰብ የሚያቀረበዉን እቃ ጽ/ቤቱ ድረስ የሚያመጣዉ በራሱ ወጭ ይሆናል፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት